በቤንሻንጉል የደረሰውን ማንንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ -ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበራዊ ድጋፍ የተሰጠ የአቋም መግለጫ


በቤንሻንጉል የደረሰውን ማንንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ -ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበራዊ ድጋፍ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
ታህሳስ 15, 2013 ( December 24, 2020)
እኛ በካናዳ የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራችን ባለፉት ጥቂት አመታት በደረሱት የዘር ተኮር ጥቃቶች ያዘንን እና የምናወግዝ መሆናችንን በተለያየ መንገድ የገለፅን ቢሆንም ፤ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመጠንም ሆነ በጭካኔው ዓይነት እየባሰ የመጣው የመተከል ዞን ሰቆቃ እጅግ አሳዝኖናል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ የአካባቢውን ችግር ለመፍታት ከአካባቢው ባለሥልጣኖች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው አዲስ አበባ እንደተመለሱ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። ድርጊቱን በጣም አሳዛኝ የሚያደርገው ጉዳይ ደግሞ በአካባቢው የመከላከያ ኮማንድ ፖስት ተመድቦ እያለ መሆኑና እና ለረጅም ሰዓታት ጭፍጨፋው ሲካሄድ በፍጥነት ደርሶ ወገኖቻችንን መታደግ አለመቻሉ ነው።
ኢትዮጵያ ከ ት.ህ.ነ.ግ. አስከፊ አገዛዝ ተላቃ በለውጥ ጎዳና ላይ ብትሆንም ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቷ ክልሎች የሚገኙ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፏል ወይም ወድሟል። ባጠቃላይ ዜጎች የለውጡን ትሩፋት እያጠናከሩ አገራቸውን ወደ ተሻለ እድገትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት በማሸጋገር ሥራ ላይ እንዳያተኩሩ በግልና በቡድን የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን በማካሄድ ሥርዐት አልበኝነት እንዲነግስ በትጋት ሲሰሩ ቆይይተዋል፣ እየሰሩም ይገኛሉ።
መንግሥት እያካሄደ ያለውን ለውጥ የምንደግፈውና የምናግዘው ሲሆን፣ የመንግሥት ቀዳሚው ሃላፊነት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ነው ብለንም እናምናለን። በዚህ ረገድ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረትም ሆነ የችግሩ መነሻ የተወሳሰበ መሆኑን የምንገነዘብ ቢሆንም፣ በአንዳንድ የአገሪቱ ክልሎች በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈጸም ወንጀሉን ለማስቆም፣ አጥፊዎችን ለመቅጣትና ሃላፊነታቸውን በተገቢው ያልተወጡ ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ አፋጥኝ እና ተገቢ የሆነ እርምጃ ተወስዷል ብለን አናምንም። ከዚህም በላይ የቤንሻንጉሉ ጭፍጨፋ በአማራ፣ በአገውና በሽናሻዎች ላይ በመነሻነት ያተኩር እንጂ በህዳሴ ግድቡና በኢትዮጵያ ሉዐላዊ ድንበር ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ መንግስትም ሆነ ዜጎች ሊያተኩሩበት የሚገባ የከፋ አደጋ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ስለዚህም እኛ በካናዳ የምንገኝ የኢትዮጵያ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበርዊ ድጋፍ አባላትና ደጋፊዎች መንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚከተሉትን የአጭር እና የረጅም ጊዜ እርምጃዎች ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡

  1. በየትኛውም ክልል፣ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ለሚፈጸም የዜጎች ጥቃት በመጀመርያ ደረጃ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ ወይም በጥቃቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ የምንግሥት ባለስልጣናት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ
  2. ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት ተጣርተው ለህዝብ ግልጽ በሆነ የፍትህ ሂደት ተጠያቂ እንዲሆኑ
  3. በተላያዩ ወቅቶች ጥቃቶች ሲፈፀሙ የመከላከያው ሃይል በቅርብ ርቀት እየተገኘ የመሆኑ ጉዳይ በአስቸኳይ ተገምግሞ መፍትሄ እንዲሰጠው
  4. በፌደራል የመከላከያ ሃይል የሚመራ እና ከየክልሉ ከሚውጣጡ ልዩ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ እንዲሁም አካባቢው ከአጥፊዎች እስኪጸዳ ድረስ ሙሉ ቁጥጥር የሚያደርግ ኮማንድ ፖስት በአካባቢው እንዲሰማራ
  5. መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ሲቪክ ተቋማት እና በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ሰብዓዊ እርዳታ በአስቸኳይ እንዲያደርጉ እና የተፈናቀሉም ዜጎች ወደ መኖሪያቸው ተመልሰው በሠላም እንዲኖሩ አስፈላጊው መሉ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣

Latest Posts

“እኔ ለሃገሬ” በሚል መሪ ቃል አርብ August 20, 2021 6:00 PM MT ላይ አስቸኳይ የገቢ ማሰባሰቢያ የዙም ፕሮግራም ተዘጋጅቷል:: በዕለቱ በካናዳ የኢትዮጵያ ሙሉ አምባሳደር ክብርት ናሲሴ ጫሊና ነዋሪነታቸው በካናድ የሆኑ ሁለት ምሁራንን ጋብዘናል:: በዚህ ወሳኝ ወቅት ሁላችንም በዕለቱ ተገኝተን ለአገራችን ኢትዮጵያ መርዳት የምንችለውን ያህል እንድንስጥ እያሳሰብን :-ለዚህም ሲባል ባዘጋጀነው ፎርም ላይ መስጠት የምንችለውን ገንዘብና contact information በመሙላ ትተባበሩን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን:: አገራችን ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!! https://forms.gle/zGtskTPuhimiLaxN7